E-ቡታጅራ

አዳዲስ መረጃዎች

የኢፌዲሪ ከተማ ልማት ሚኒስትር እና የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የቡታጅራ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የቀጥታ አገልግሎት አሰጣጥ ምልከታ አደረጉ።

(ቡታጅራ ጥር 26/2017 የመንግስት ኮሙኒኬሽን)በምስራቅ ጉራጌ ዞን የቡታጅራ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የቀጥታ አገልግሎት መስጫ (online service delivery) ይፋ አድርጓል።
hint=WWW.butajiramun.gov.et:81

አገልግሎቱ ተገልጋዮች ቤታቸው ሆነው በተለይም የአንድ ማዕከል የትኛውንም አገልግሎት ማግኘት እንደሚያስችል ተገልጿል።

የክልሉ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎትና የሰው ሀይል ልማት ስታንዳርዳይዜሽን ምዘና ዳይሬክቶሬቶ ዳይሬክተር  ኃላፊ ተፈራ ስሜ (ዶ/ር) ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎትን ለማዘመን በሚደረገው ርብርብ በተለይ የመሬት ልማት፣የግንባታ ፍቃድ እና የማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ ዘርፎች ላይ በቀጥታ አገልግሎቱ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ መሆኑን አረጋግጠዋል።

በቀጣይም ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን ከወረቀት ንክኪ ነፃ ለማድረግ የቴክኖሎጂ አሰራር ትግል ወይም ጥረት እንደሚያስፈልግ አብራርተዋል።የተገልጋዮችን የጊዜና የጉልበት ባስቀረ መልኩ በቤታቸው እንዲያገኙ የሚያስችል በመሆኑም አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።

የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎትን ለማዘመን ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ መሆኑ በውይይቱ ተመላክቷል።
የከተማዋ ነዋሪዎች ቤታቸው ሆነው በቀጥታ የኦንላይን አገልግሎት ማግኘት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ቅድመ ዝግጅት መደረጉም ተገልጿል።

የማዘጋጃ ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ተስፋዬ አህመድ የቴክኖሎጂ አገልግሎት ለማህበረሰቡ የሚኖረውን ፋይዳ መነሻ በማድረግ የተጀመረ እንደሆነ ገልፀው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

የማዘጋጃ ቤቱ ምክትልና የማስፈፀም ዘር ኃላፊ ከድር ሁሴን የከተማዋ ነዋሪ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን የሚያስችል እንደሆነ ገልፀው የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።
hint=WWW.butajiramun.gov.et:81

በከተማ ልማት ሚኒስቴር የከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ስታንዳርዳይዜሽን ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ፍቃዱ ሳህሌ፣በክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ስታንዳርዴሽን ማዘመን ዳይሬክተር አቶ አብደላ ሳሊሀ፣የምስራቅ ጉራጌ ዞን  ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ም/መምርያ ኃላፊና የማስፈፀም አቅም ግንባታ መሰረተ ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ መሀመድ ኢብሮ ተገኝተዋል።

ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን፦ቴሌግራም https://t.me/ButajiraCommunication/58ፌስቡክ https://www.facebook.com/buta1921/ዩቲዩብ https://youtube.com/@butajiracommunication189ትዊተር https://mobile.twitter.com/ButajiraBኢንታግራም https://www.instagram.com/butajirab